Monday, July 25, 2011

The latest Information to the public from The USt.Michael PRSCommette...



Information Extarcted from MERWA... on 7-25-2011


የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

ውድ ምእመናን እንደምን ከረማችሁ እኛ በፈጣሪ ቸርነት እስካሁን አለን። ምነው ጠፋችሁ?  ብላችሁ ለጠየቃችሁን መልእክት ለጻፋችሁልን ሁሉ አለን ክብሩ ይስፋ ለመድኅኒዓለም  እንላለን። ከ ሁለት ቀን በፊት የ5ኛው districte ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወይዘሮ  ጥሩአየርና  በአቶ ዳግም በተመሰረተው የቦርድ አባላት ያለአግባብ የስልጣን አጠቃቀም ክስ ላይ ብይን መስጠቱን ለአንባብያን መናገር እንወዳለን። መረዋ  ብይኑን ሙሉ ለሙሉ አንባብያን እንድታነቡት ሲያቀርብላችሁ እራሳችሁ አንብባችሁ ግንዛቤ  እንድትወስዱ በማሰብ ነው። በተከበሩት ዳኛ ኤልዛቤት ሜየር የተጻፈው የብያኔ  ትችት እንደሚያስረዳው፣ ይግባኝ ባዮቹ ከሳሾች የቤተክርስቲያኑ የቦርድ አባላት አላግባብ ስልጣናቸውን ተጠቅመው መተዳዳሪያ  ደንቡን መቀየራቸው አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው መክሰሳቸውን ተነተርሶ የቀረበ  ክስ መሆኑን አስታውሶ ክሱ በመብት መደፈር አኳያና የቤተ ክርስቲያኑ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ አንስቶ ቢሆን ኖሮ ፍርድ ቤቱ መግባትና መወሰን ይችል እንደነበር አውስቶ ነገር ግን በመተዳደሪያ  ደንቡ ላይ ብቻ ያተኮረ ስለሆነ ይህ ደግሞ በውስጥ መፈታት ያለበት እንጂ ፍርድ ቤት በእምነት ውስጥ ጣልቃ  መግባት የለበትም የሚል ብዙ ተመሳሳይ የቆዩ ውሳኔዎችን በመጥቀስ የበታች ፍርድ ቤት ቦርዱ የመተዳደሪያ  ደንቡን መቀየር ይችላል ብሎ  የበየነውን ውሳኔ አጽንቶ ወስኗል። የቤተክርስቲያን ቦርድ አባላት ክሱ በውሸት የተመሰረተ  የቦርድ አባላትን ስራ ለማስፈታት የተመሰረተ  መሆኑን የይግባኝ ፍርድ ቤቱ እንዲወስንላቸውና  ካሳ  እንዲጥልላቸው ያቀረቡትን ሳይቀበለው ቀርቷል።

ለምን ታዲያ የንብረት ይገባኛል ጥያቄውን ከመጀመሪያው አላነሳችሁም ብለን ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ  ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች የነገሩን ቢኖር ከመጀመሪያው ይህ  ሃሳብ ቀርቦ የከሳሾች ፍላጎት የቤተክርስቲያኑን አባላት መብት ለማስጠበቅ እንጂ ለመበታተን ስላልነበር ሃሳቡ ተነስቶ  ውድቅ እንደተደረገ ለመገንዘብ ችለናል።

ባሁኑ ሰዓት ግን የንብረት ይገባኛል ክስ ቢመሰረት ማንም ምእመን ሊቀበለው የሚችል ለመሆኑ በሂደት በቤተክርስቲያኑ አባላት ላይ የደረሰው በደልና  አሁን ቤተክርስቲያኑ ያለበትን  በማሰብ መናገር ይቻላል ብለው እንደሚያምኑም ለመረዳት ችለናል።

መረዋ  በእትምት ጅምሩ ላይ የጠቆማቸው ሁሉ ተራ  በተራ ተፈጻሚ ሆነዋል።

ካህናት ተባረዋል
አባላት ተበትነዋል
የስደት ሲኖዶስ ከበራፍ ቆሞ እየጠበቅ ነው
እምነት ሳይሆን ስልጣን፣ አባላት ሳይሆኑ ተመራጮች ፈላጭ ቆራጭ ሆነዋል።
የነበረው ገንዘብ መንምኗል፥
ፖለቲከኞች መሰባሰቢያ  ሲያገኙ አማንያን ከስብሰባ  ታግደዋል
በእምነት ሳይሆን በፖሊስ ለማስፈራራት ተሞክሯል
የቦርድ አባላት ወንጀል በይቅርታ  ሲታለፍ ግለሰቦች ወደፍርድ ቤት በመሄዳቸው ወይም ቦርዱ የሚደረገውን በመቃወማቸው ነፍሰገዳይ ዝሙተኛ ሌባ ሴሰኛ እየተባሉ ከእግዜር በተላከ ቁጣ የሞት ፍርድ ሳይቅር እንደተፈረደ  ሁሉ ተጽፏል።
በአባላት ላይ የክፍያ  ጫና  ተጥሏል።
በዘር እንዲከፋፈል ተደርጓል
የስደት ሲኖዶስ አባላት ሰፈር ተወለጆች እንዲጠናከሩ ሲደረግ ሌሎች በዘራቸው ተወንጅለዋል።
ሲፈርዱ የነበሩ ፈራጆች ዛሬ ተፈርዶባቸዋል።
የቤተክርስቲያን መስራቾች በመመስረታቸው ተነቅፈዋል ወዘተ

ልንል የፈለግነው ያላሰብነው አዲስ ክስተት አልተፈጠረም ለማለት ነው
ባጋጣሚ ትላንትና የደረሰን ዜና  ደግሞ  ወጣት የቤተክርስቲያን ልጆች ጥያቄ  አቀረባችሁ ተብለው መባረራቸውን መስማታችን ነው። ጥያቄው ምን ነበር ስንል
ለምን የረባ  ምሳ አትሰጡንም?
ገንዘብ የለንም ካላችሁ ለምን መብራትና ቴሌቪዥን ግዢ ሄዳችሁ?
በእኛ ስም ከበጎ አድራጊዎች የተገኘ ገንዘብ የት ገባ?
ሳንማር የምንመረቀው እንዴት ነው? የሚሉ እንደ ነበሩ ለመረዳት ችለናል።

እነዚህ  እዚህ የተወለዱና  ያደጉ ሕጻናት ደግሞ ፖለቲካውም አይገባቸው ውሸትም አይዋጥላቸው፥

መረዋ ላለፉት 5 ዓመት ከልባቸው ለእውነት ለፍትህ ለመብት ለታገሉ ምእመናን በሙሉ ያለውን አክብሮትና አድናቆት እየገለጸ ወደፊትም በዚህ መልክ ለሚነሱና ካሁን በኋላ  የንብረት ጥያቄ  ለሚያነሱ  ሁሉ ድጋፉን ለመለገስ ወደ ኋላ  እንደማይል ካሁኑ ቃል ይገባል።

የማንም መብት ሲጣሰ የግል መብት እንደተጣሰ  መቁጠር ትክክለኛ  ውሳኔ  ነው።

የሚሸነፍ ሰው ለመብቱ የማይነሳ ብቻ  ነው።

ሰላምና ፍቅር ለሁላችሁ ይሁን፥
http://www.5thcoa.courts.state.tx.us/cgi-bin/as_web.exe?c05topin.ask+D+510527
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንዳለ  ለማንበብ  

Thursday, March 24, 2011

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ PR witnessed at court hearing

Compiled and posted for your edification FROM a true resource MEREWA
   የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ  
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE   Public Relations Office Staff has witnessed on this day 3-23-2011 the Court Hearing.
 
After asking, pleading and begging for a meeting with the St. Michael Church Board and Board Members for over two years (22 June 2008 to 15 January 2011)  we as a committee have agreed to attend the legal venue. We have come to conclusion that this is the only way the board members can understand.  This committee stands for the majority public. Elected by the public. We will update the public as information is avialable. We will announce when we are completing our job. Please, read the following exerpts from መረዋ MEREWA:

የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ

 
እንደምን ከረማችሁ ምእመናን

የተለየ ነገር ሳይኖር በተደጋጋሚ እናደርገው እንደ ነበረው በተከታታይ ባለመውጣታችን ምን ነካችሁ?  ላላችሁን። መረዋን አትግደሉብን ብላችሁ ለጠየቃችሁን። መረዋ ላይ ካልወጣ እውነት አይደለም ላላችሁና እምነት ለጣላችሁብን ሁሉ ምስጋናችን ወሰን የለውም። ዋሽተን ከምንከበር ይልቅ እውነቱን ተናግረን ብንወገር እንደምንመርጥ መናገር ደግሞ እውነትነቱ አንደማያጠራጥር ምስክሮቻችን እናንተ  ናችሁ።  በመሆኑም እንደ ተለመደው የዛሬን  የፍርድ ቤት   ውሎ እናካፍላችሁ
 
ባለፈው እትምታችን እንደ ነገርናችሁ  የዛሬው ቀጠሮ በ 192 የካውንቲ ችሎት በዳኛ ስሚዝ ፊት የተደረገ ክርከር ነበር። ባለፈው እረዳት ዳኛ የቦርዱ ሹማምንት ከከሳሾች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመመለስ ብሎም የቤተክርስቲያኑን ዶሴዎች የማሳየት ግዴታ አለባችሁ ብለው የወሰኑትን ውሳኔ በመቃወም የቦርዶቹ ጠበቃ  ለዋናው ዳኛ ስሚዝ ይግባኝ ማለታቸው ይታወሳል። የዛሬው ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ባለፈው በቦርዱ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዳነሳላቸው የዘገብነው ጉዳይ ነው።

በዛሬው  እለት የተከሳሾች ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ በ march 21st ያስገቡት  ማመልከቻ ለከሳሾች ጠበቃ እንዳልደረሳቸው ለፍርድ  ቤቱ ሲናገሩ ፍርድ ቤቱ ለምን? ብሎ  የተከሳሾችን ጠበቃ  ሲጠይቅ መልሳቸው በfax ልከናል የሚል  ነበር። ፋክስም እንዳልደረሳቸው የተናገሩት የከሳሾች ጠበቃ ባላዩት ማመልከቻ  ላይ ምንም ውሳኔ  ሊሰጥ  እንደማይቻል ተናግረው ዳኛው ተስማምተዋል። ዳኛው የይግባኝ  ሰሚ ፍርድ ቤት በሃይማኖት ጣልቃ  አትግቡ ብሏልና ለምን ጉዳዩን አየዋለሁ? ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የተከሳሾች ጠበቃ  እኛም የምንለው እሱን ነው ብለው ሲመልሱ፣ የከሳሾች ጠበቅ ግን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወሰነው በእገዳው ላይ እንጂ በክሱ ይዘት ላይ አይደለም በማለት ተከረክረው ለዚህም በውሳኔው መደምደሚያ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን 
ፍሬ ሃሳብ ሳይተችበት ለዳኛ ስሚዝ ማስተላለፉን ጠቅሰዋል። የከሳሾች ጠበቃ  አያይዘውም አሁንም ቢሆን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ አልስማማም ያ  እንዳለ  ሆኖ ለክቡር ፍርድ ቤቱ ልጠይቅ የምፈልገው እነዚህ የቦርድ አባላት እንደ ፈለጉ ሕግ መቀየር ከቻሉ ነገ  አዲስ ሕግ አውጥተው ንብረቱን ወስደው ቤተክርስቲያኑን ሸጠው ወደ ጃማይካ  ቢሄዱ ምን የሚያግዳቸው ነገር አለ። እዚህ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ለምን ያስፈልጋል?  ፈላጭ ቆራጩ ቦርድ እንጂ አባላት ምንም መብት የላቸውም። የከሰሰ  ከአባልነት ይባረራል ካሉ። አባል ለመሆን ማመልከቻ  አስገብቶ  የቦርዱን ፈቃድ መጠየቅ ካለበት ስልጣኑ የምእመናን ሳይሆን የቦርዱ ነው ብለዋል። ስለሆነም ቦርዱ ነገ  ሕጉን  ቀይሮ ምንም ማድረግ ይችላል አባል ምንም መብት የለውም ብለው ለፍርድ ቤቱ አሳስበዋል። በተጨማሪም ይህ ቤተክርስቲያን የ  501 C ፈቃድ ያለው እስከ ሆነ ድረስ  የፌድራልና የስቴት ሕግ የመከተል ግዴታ  አለበት በሃይማኖት ሽፋን ወንጀል መስራት አይችሉም ብለዋል። የተከሰሱት የቦርድ አባላት የራሳቸውን ሕግ እንኳን የማያከብሩ ናቸው ለዚህም የምርጫቸውን ሁኔታ መመልከት ይቻላል በማለት ተከራክረዋል። የተከሳሾች ጠበቃ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከወሰነው ውጭ ፍርድ ቤቱ ምንም ማድረግ አይችልም ብለው ዛሬውኑ ክሱ ተሰርዞልን እንሰናበት ብለው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር።

በመጨረሻም ዳኛው ሁለቱ ጠበቆች ተስማምተው የመከራከሪያና  የፍርድ ሃሳባቸውን ከዚህ በፊት ከነበሩ ተመሳሳይ  የተለያዩ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ጋር እንዲያቀርቡላቸው ሁለት ሳምንት ሲሰጡ ስምምነቱን አስመልክቶ የተከሳሽ ጠበቃ ጽፈውና ፈርመው ለከሳች ጠበቃ እንዲያሳልፉ የከሳሽ ጠበቃ ደግሞ ፈርመው ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀረቡ ነግረዋቸዋል።

ዳኛው የሁለቱን መከራከሪያ ነጥብና የፍርድ ሃሳብ ካዩ በኋላ ማስረጃ መስማት እንደሚያስፈልግም ሆነ ክርክሩን ለመክፈት ወይንም ለመዝጋት ውሳኔ  ለመስጠት ለ APRIL 15 ቀጠሮ  ሰጥተው የእለቱ ችሎት  ተፈጽሟል።

በተጨማሪም በወይዘሮ ጥሩአየር እና  በአቶ  ዳግም ከሳሽነት ተመስርቶ በዳኛ  እስሚዝ የቦርዱ አባላት ካለ አባላት ፈቃድ ሕጉን መቀየር ይችላሉ ብለው የበየኑት ብያኔ  የሚታወስ ነው። ውሳኔውን በመቃወም ከሳሾቹ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ  ማለታቸው ይታወሳል። ስለሆነም ጉዳዩን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እያለ ከሳሾች ፍርድ ቤቱ ያለውን መረጃ ተመልክቶ  ውሳኔ  ይስጠን ቢሉም የቦርዱ ጠበቆች የለም የቃል ክርክር እንፈልጋለን በማለታቸው የቃል ክርክሩን ለማዳመጥ ጉዳዩ ለመጭው MAY 4,  2011, 1:00 P.M., 5th District Court of Appeal of Texas, 600 Commerce, George L. Allan Bldg. Suite #200   መቀጠሩን ልንነግራችሁ እንወዳለን። 
ማንኛውም የቤተክርስቲያን ምእመን  በፍርድ ቤት በመገኘት ክርክሩን ማዳመጥ  እንደሚችል ስንነግራችሁ በደሰታ  ነው።
የቦርድ አባላት የማያልቅ ገንዘብ ስላላቸው ብዙ የማቆያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ትላንት ፍርድ ቤት የተነገረ ሲሆን፣ መብታቸው የተደፈረው ምእመናን ደግሞ  ፈጣሪንና ደጋፊዎቻቸውን ይዘው መታገላቸውን እንደማያቆሙ ከሂደቱ መገንዘብ ይቻላል::
  መረዋ ለምእመናን የሚጠይቀው ነገር ቢኖር!  
  መብት የሌለው አባልነት ምንድነው?       የሚል ይሆናል።
 
 መረዋም የዛሬውን ዘገባ  በዚሁ ያበቃል::
 
United St. Michael Peace Seeker Resolution Committee will follow up the truth and justice. 
 The public has imposed responsibility and we will update every move there is.  Our MOTO is: Honest, faith, peace, justice, mercy, love, humble, integrity, pride.
 
Public Relation Office.

Friday, January 28, 2011

United St. Micheal Church Peace Resolution Seekers Committee 3rd General Meeting 1--23-2011, Report from PR

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ                 UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE 
       Meleket4u@gmail.com

1-23-2011
                                          ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ

የዛሬውን አጠቃላይ ስብሰባ በ15:15 ፒ ኤም ም/ሊቀመንበሩ አቶ ግርማቸው አድማሴ ስብሰባውን በቄስስ መስፍን ደምሴ ቡራኬ በመስጠት በአንድነት በፀሎት ከፍቱልን። 5 ኤም ስብሰባው ተዘግቷል።

ከተሰጡትም ገንቢ አስተያየቶችና መልዕክቶች መካከል፤
ሀ. የኮሚቴው ዋና ሥራ የሆነው የሕግ አገልግሎት ጉዳይን በተመለከት መሰረታዊ ጥያቄዎችና ዓላማዎች ግልፅና አጭር በሆነ መልክ ለምዕመናን መግለጫ እንዲሰጥ።
ለ. የመልአከ ሣህልን በሥራ ጉዳይ ምክንያት ወደ ሌላ ግዛት መሄዳቸውን አስመልክቶ በ 1-28-2011 በሚደረገው የሽኝት ዝግጅት ላይ ከዓርብ ጉባኤ ጋር በመቀናጀት አሰኛኘት እንዲደረግላቸው።
ሐ. በቅርቡ በሚካሄዱት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች 2-7-2011፣ በ3 ፒ ኤም እና 2-10-2011፣ በ9 ኤ ኤም ላይ መገኘት የሚችሉ ምዕመናን አንዲገኙ።
መ. “ቤተክርስቲያን ተከሷል” የሚባለው የተዛባ ውዥንብር የሚወገድበት ትክክለኛው የፍትሕ ጥረት ለምዕመናኑ በመግለፅ የሚረዱበት መንገድ እንዲፈጠር።
ሠ. በዓርብ ጉባኤ እየተዘጋጀ ባለው ሦስተኛ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ኮሚቴው ትብብሩን እንዲያደርግና መድረኩንም በመጠቀም ለሕዝቡ መልእክት እንዲያዘጋጅ።
ረ. የሕግ ጉዳዩን በተመለከተ ለሚያስፈልጉት የኃሳብና የገንዘብ ዕርዳታ ቅንጅትና ትብብር በመላ ምዕመናኑ የሚካሄድበትን።

ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Wednesday, January 12, 2011

Message from URC Public Relations Office "MELEKET4U"

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ  
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
                     “መለከት”       
     meleket4u.blogspot.com
“ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ ጥሪ”
(የሕዝብ አደራ መጠበቅ ስለ አለብን፣ በተፈጠረው ወቅታዊ አጋጣሚ ችግሮችና ሐዘኖች ምክንያት የተሰረዘው የምዕመናን ስብሰባ ጥሪ እንደገና ይቀጥላል። ብርታቱን ለሁላችንም እግዚአብሔር ይስጠን።)
ቀኑ፡-ጥር 15 ቀን 2003 እሁድ
January 23, 2011, Sunday
ሰዓት፡-1፡00 ፒ ኤም፡ምሳ አለ።
ቦታው፡- Dream Club, 7035 Greenville Ave #E, Dallas, TX 75231-5109 (214) 368-4981 ወይንም (469) 879-8650