Saturday, December 18, 2010

United St. Micheal Church Peace Resolution Seekers Committee Postpond the 3rd General Meeting that will be held on 12-19-10

United St. Micheal Church Peace Resolution Seekers Committee Postpond the 3rd General Meeting that will be held on 12-19-10, 1:00 p.m. at Dreams Club for mid-January 2011.

       የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
12-16-2010
                “መለከት የጠራው”     “ጠቅላላ የምዕመናን የስብሰባ ጥሪ ቀን መተላለፍ”http://www.meleket4u.blogspot.com/                                           meleket4u@gmail.com
በኮሚኒቴአችን አባላት በደረሰው ድንገተኛ ሐዘን ምክንያት፣ የስብሰባውን ቀን እስከ ጃኑዋሪ 2011 አጋማሽ ድረስ ያስተላለፍነው መሆናችንን እናስታውቃችኋለን።
በደረሰባቸውም ድንገተኛ አደጋም የኃዘናቸው ተካፋይ መሆናችንንም ከልብ እንገልፃለን።


 ኮሚቴው።

የስብሰባ ቀን ጥሪ መተላለፍ

የተባበሩት የቅዱስ  ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ 
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS  COMMITTEE 
http://www.meleket4u.blogspot.com/                                                MELEKET4U@GMAIL.COM

በመሃከላችን በተከሰተው ያልተጠበቀ ድንገተኛ ሐዘን ምክንያት በነገው እለት እሑድ ከቅዳሴ  በኋላ  በ 1:00 PM  ተጠርቶ  የነበረው የምእመናን ስብሰባ ወደ እሚመጣው ወር አጋማሽ እንዲተላለፍ የተወሰነ መሆኑን ለአባላትና  ለደጋፊዎቻችን እናስታውቃለን። ስብሰባው መቼና የት እንደሚሆን ወደፊት እንነግራችኋለን።

በዚህ አጋጣሚ የዚህ ኮሚቴ  አባላት በደረሰው ሐዘን ከልብ መነካታችንን እየገለጽን ወጣቱን ከመላእክት ዘማርያን እንዲቀላቅለው ቤተሰቦቹን ደግሞ ብርታትና  መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንለምናለን።

ኮሚቴው




Thursday, December 9, 2010

Reporting to St. Michael's MeMenan the result of Elders meeting with UR Commette

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
ይህ ሪፖርት ከኮሚቴው የተላፈ ነው።
12-04-10
የቅዱስ ሚካኤል አስተዳደር ቦርድ ሰላምና ለሽምግልና እምቢተኝነቱን በድጋሚ አረጋገጠ።
የተከበራችሁ ውድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተሰቦች አንደምን ሰነበታችሁ።
ባሇፈው በ9/23/10 ከቤተክርስቲአናችን ሰላም ወዳድና ያለትን ችግሮች ሁለ በሰላም መንገድ መፍታት ይቻላል በሚለ ኃይሎችና በእኛም ኮሚቴ ድጋፍ አግኝቶ በአቶ ሰይፉ ይገዙ ሰብሳቢነት የሚመራ የሽምግልና ኮሚቴ ሥራውን መጀመሩን መግለጻችን የሚታወስ ነው። ይህ የሽምግልና ኮሚቴ የቦርዱ የሚለ ጥቂት የሰላም መንገድ ምን እንደሆነ ያልገባቸው ግለሰቦች ሲፈጥሩት የነበረውን ሁካታ እያዳመጥን ተጨባጭነት እስኪኖረው ድረስ ሪፖርት ከማቅረብ ተቆጥበን ነበር። አነሆ አሁን ደግሞ በመጨረሻ የሽማግሌዎቹ ኮሚቴ ያክናወኑትን ጉዳይ ለቅዱስ ሚካኤል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለማስረዳት በ12/1/10 ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ በክራውን ፕላዛ ሆቴል በተስማማንበት መሰረት ተሰባሰብን የሽማግሌዎቹም ኮሚቴ በአቶ ሰይፉ ይገዙ መሪነት አቶ ዳኜ፣ ዶክተር ታየ፣ አቶ ጌታቸው፣ አቶ ኪዳኔና አቶ በትሩ ሲሆኑ ሰብሰባውም በጸሎት ተጀመረ ሰባሳቢው አቶ ሰይፉ አጠቃላይ ሁኔታውን አቅርበው ሲጨርሱ ሌሎቹም ሽማግሌዎች በየተራ የየራሳቸውን አስተያየት አስደምጠውናል::
ውድ የሚካኤል ቤተሰቦች ሆይ! የተከበሩት ሽማግሌዎች ያዓቅማቸውን ያህል መጣራቸው ግልጽ መሆኑን ብንገነዘብም በሁለም መንገድ ሰላምን የሚሸሸው (የማይፈልገው) ቦርድ የቤተክርሰቲአኑን አዛውንቶች ወደ ሁሇት ወር ካደከማቸው በኋላ የምቢተኝነቱን መልስ ሰጥቶአቸዋል። በተጨማሪም የቦርዱ አባላት በቤተክርስቲአናችን ውስጥ ምንም ችግር እንደሌሇ ችግርም አሇ ከተባሇም አሁን በብዙ ስራ ስሇተጠመድን በሚቀጥሇው ዓመት ጉዳዩን እናየዋሇን እንዳለዋቸው ሲነግሩን በጣም አዘንን እናም በሽታውን የማያውቅ በሽተኛ ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደሌሇው ቢአውቅ ብልህነት ነበር እንላሇን!
ውድ የሚካኤል ቤተሰቦች ኮሚቴአችንም አዛውንቱን ለሞከሩት ሙከራ ከልብ አመስግኖ እንዲሁም እምቢተኛው ቦርድ ለሰጣቸው መልስ ምስክሮቻችን እንደሆኑ ከአስረዳን በኋላ ስብሳባው በጨዋነት በጸሎት ተፈጽሞአል።
ለሰላምና ለፍትሕ የሚደረገው ጥረት ይቀጥላል። ይዘገያል እንጂ ፍትሕ መገኘቱ፤ እውነቱ መውጣቱ አይቀርም።
ኮሚቴው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

Saturday, December 4, 2010

የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
“መለከት” “ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ ጥሪ”
http://www.meleket4u.blogspot.com/ meleket4u@gmail.com
ታኅሣሥ 10, ቀን 2003
December 19, 2010, 1:00p.m.
ምሳ! የጾም ምግብ አለ! ቦታው፡- Dreams Club, 7035 Greenville Ave # E, Dallas, TX 75231-5109 (214) 368-4981 ወይንም (469) 879-8650

Sunday, November 14, 2010

Message from URC Public Relations Office

 የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ  
           UNITED ST. MICHAEL CHURCH RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE                   
                  
ካለፈው የቀጠለ።

የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ክፍል በሂደት ለሕዝብ/ለአንባቢያን የሚያቀርበው ያለ ጊዜ ገደብ ስለሆነ የሂደቶቹን እንቅስቃሴ በአግባቡና በወቅቱ እናቀርባለን። የሃሳብ ወይንም ኮሜንት መስጫ ቦታ ስላለን ተጠቀሙበት።

የተከበራችሁ ውድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተሰቦች አንደምን ሰነበታችሁ።
አንደምታስታውሱት ባለፈው በ9/23/10 ከቤተክርስቲአናችን አባላት መካከል በአቶ ሰይፉ ይገዙ የሚመራ የሽምግልና ኮሚቴ ጋር ኮሚቴአችን ተሰብስቦ አንደነበር በዚሁ ጦማር ላይ አስነብበናችሁ ነበር። አነሆ አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ወራት የሽምግልናው ኮሚቴ አባላት የተወስኑ የሚካኤል አባላትና የሚካኤል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በየመስመራቸው ሽምግልናው ይሳካ ዘንድ ውይይቱን ቀጥለዋል ምንም አንኩዋን የቤተክርስቲያኑ ቦርድ አንካሳ ምክንያት አየደረደረ ቢገኝም ውይይቱ አንደቀጠለ ነው። በቅርቡም በሽምግልናው በኩል ያለው ሁኔታ በአጠቃላይ አናቅርብላችኋለን አስክውዚያው ቸር ይግጠመን።

ከሕዝብ ግንኙነት ክፍል
           

Saturday, September 25, 2010

ሳምንቱን ካጋጠመን

የተከበራችሁ፡ ውድ፡ ምዕመናን፡

     እንደሚታወቀው፡ የቅዱስ፡ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን፡ ችግር፡ መፍትሄ፡ ለማፈላልግ፡ እንድንጥር፡ ከመረጣችሁን፡ ጊዜ፡ አንስቶ፡ የጣላችሁብንን፡ አደራ፡ ለመወጣት በጥንቃቄ፣ በቆራጥነትና፣ በቅንነት፡እየሰራን፡ እንደሆነ፡ ልናረጋግጥላችሁ፡  እንወዳለን።  ችግሩን፡ ለአንዴም፡ ለሁሌም ለመፍታት፡ የምንችለውን፡ ሁሉ፡ በሁሉም፡ አቅጣጫ፡  እየጣርን ነው፡፡ ታዲያ፡ ሰሞኑንም፡ ከቤተክርሰቲያናችን፡ አባላት፡ መካከል፡ የተወሰኑ፡ግለሰቦች፡ ሰላም፡ መስፈን፡ ይኖርበታል፡ ከሚል፡  መርህ፡ በመነሳት፡ አዛውንቶችን፡ አነጋግረው፡ እንደነበረና፡ ሽማግሌዎቹም እንዚህን ቡድኖች ባነጋገሩ ማግስት የኛን ኮሚቴ ለማነጋገር ወስነው መበተናቸውን ለማወቅ ችለን ነበር። ግለሰቦቹን ያነጋገረው፡የሽማግሌዎቹ፡ ኮሚቴ አባላት፡ መካከልም፡ ከፊሎቹ፡ ለቤተክርስቲአናችን፡ ብዙ፡ ግልጋሎት፡ ያበረከቱ፡ በመስራችነታቸው፡ የሚታወቁ ባካባቢያችን፡ የቆዩ፡ የችግሩንም፡ አነሳስ፡ በሚገባ፡ ሲጀመር፡ ጀምሮ፡ የተመለከቱ፡ አንዳሉበትም፡ ለመረዳት ችለናል። ሽማግሌዎቹ፡ እነዚህን ሰላም እንፈልጋለን የሚሉትን ቡድኖች ባነጋገሩ ማግስት፡ሁለት፡ ቀን፡ባልበለጠ፡ ጊዜ፡ውስጥ፡ ተሰብሰበን፡ ከነርሱ፡ ጋር፡ መወያየት፡ እንድንችል፡ በሊቀመ ንበርችን፡ በኩል፡ ጥያቄ፡  አቀረቡ፡፡ አኛም፡ ጊዜ፡ ሳናባክን፡ ተሰብስበን፡ ከሁለት፡ ሰዓት፡ በላይ፡ ጉዳዩን፡ ከሁሉም፡ አቅጣጫ፡ መርምረን፡ ከጉዳቱ፡ ይልቅ፡ ጥቅሙ፡ እንደሚያመዝን፡ በመገንዘብ፡ በአንድ፡ ድምጽ፤ ተቀብለን፡ ሽማግሌዎቹን፡ ሐሙስ፡ በ6፡00PM (9/23/10) ለማነጋገር ተስማምተን በተባለው ሰዓትና ወቅት ሽማግሌዎቹን አነጋግረናል።

 ውይይቱ፡ በአካል፡ በቅዱስ፡ ሚካኤል፡ የስብሰባ፡ አዳራሽ፡ ውስጥ፡የተካያደ ሲሆን መልካም፡ ጅማሮ፡ የታየበት፡ የሁለት፡ ሰዓት ስብሰባ ነበር። ቀጣዩም፡ ስብሰባ፡ የመልክተኞቹ፡ ኮሚቴ፡ ከቤተክርስትያኑ፡ የቦርድ፡ አባላት፡ የይሁንታ፡ ደበዳቤ፡ ከዚያም፡ ለመላው፡ የቅዱስ፡ ሚካኤል፡ ምአመናን፡ በይፋ፡ ከተነገረ፡ በኋላ፡ እንደሚሆን አስታውቀናቸው፡ በቅን፡ መንፍስ፡ ተደምድሟል።

ድ፡ ምአመናን፡ ሆይ!

የቅዱስ፡ ሚካአኤል፤ ችግር፤ የመፍትሄ፤ አፈላላጊ፤ ኮሚቴ፤  የምናደርገውን፤ ጉዞ፤ ሁሉ፤ አንድ፤ በአንድ፤ በጥንቃቄ፤ አንደምናሳውቃችሁ ቃል በገባንው መሰረት ይህንንም ከሌሎች ከመስማታችሁ በፊት ከኮሚቴው እንድትሰሙት በማለት አውጥተነዋል። ወደፊትም አቅማችን፡ በፈቀደው፤ ፍጥነት፤ ሁሉንም ሂደት እንድታውቁት፡ እንደምናደርግ ቃል እንገባላችኋለን።

የሕዝብ፡ ግንኙነት፡ ኮሚቴ፡

የልኡል፡ አግዚአብሔር፡ እረድኤት፡  ይታከልበት!!

Saturday, September 18, 2010

የሰላም ጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

ከስብስቡ ሊቀመንበር የተላከ  መልእክት

የሰላም፤ የአንድነት፣ የፍቅር  ጥረቱ አሁንም እንደቀጠለ  ነው። የምንመኘውን የምንፈልገውን ዘላቂውን ሰላም፤ አንድነት፣ ፍቅር በቤተክርስቲያናችን  ብሎም በሕብረተሰባችን ልናመጣ የምንችለው የተለየዩ  የመፍትሄ  ሃሳቦችን የያዙትን፡ በዳይ ነው የተባለውንም ሆነ ተበድሏል የተባለውን አቀራርበን ውይይት ማድረግ ሲቻልና ብዙሃኑ የተቀበለውን ማስፈጸም ስንችል ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር ለችግራችን ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት ሁላችንም የሚያስማማንን መንገድ የመፈለግ ግዴታ አለብን። ይህ ደግሞ ብስለትን፤ ቅንነትን፤ ሐቀኝነትን፣ መተማመንን ይጠይቃል። ፈረንጆቹ እንደሚሉት(MY WAY OR  THE HIGH WAY ) ወይም እኔ  ያልኩት ካልሆነ እሞታለሁ የሚል አመለካከት ካለ ግን የተነሳንበትን የመወያየቱን መርህ ይገድለዋል።

ይህንን ካልን ዘንዳ!!በዚህም በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተነሳው አለመግባባት ደረጃው ይለይ እንጂ ከቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ዙሪያ "በደል ደረሰብን፣ መብታችን ተነካ፣ መተዳደሪያ ደንቡ ተሸረሸረ፣ የብዙሃን ድምፅ ታፈነ፣ ሃሳባችን አልተስተናገደም ወዘት በማለት የሚያስቡ ግለሰቦች ለችግራቸው መፍትሄ ነው ያሉትን አቅርበው መወያየት ችለዋል። በውይይቱም ተማምነው የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም በቅተለዋል። አስተማማኝ ሁኔታም እስኪፈጸም  ድረስ  የተነሱበትን ዓላም እንደማይስቱ አሁንም ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር እንደሚታገሉ፣ ሁላችንም ይህንን መርህ ከተከተልን ደግሞ ወደ  ነበርንበት መመለሱ ሕልም እንደማይሆን ያምናሉ።  

የአንድ አካባቢ ስብስብ ወይንም በብዙሃን ድምፅ የሚተዳደር አካል ለተለያዩ ሃሳቦች መፍትሄ የሚያገኘው ብዙሃኑ ተስማምቶ በተቀበለው ሃሳብ ሲመራ መሆኑን አንጠራጠርም። ይህንን አማራጭ የሌለውን አካሄድ መከተል ደግሞ ግዴታ ነው እንላለን።  እስከዛሬ በግልም ሆነ በቡድን በጽሑፍም ሆነ በቃል የተነገሩ ሃሳቦች ሁሉ  በእንዲህ ያለ አጠቃላይ ሁሉን አቀፍ ተደጋጋሚ ስብሰባ መቋጨት አለባቸው ብለን እናምናለን።  

የዚህ ጦማር  አጀማመር ደግሞ ያለምንም መደባበቅ በእውነት ላይ ያተኮረ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ሌሎች እንዲረዱት ሃሳቦችን ማንሸራሸር እንዲቻል ከሚያገኘው ጭብጥ በመነሳት አንባቢው ፍርድ መስጠት እንዲችል ለመርዳት ጭምር ነው።

የጦማሩ ባለቤቶች በ 200አባላት የተመረጠው የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴ ሲሆን፣ ኮሚቴው እስካሁን ያከናወነውን እያደነቅሁ በዚህም መስክ ጥሩ ተግባር እንደሚያሳይ ጥርጥር የለኝም። አባላቱም የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ጦማሩ የእውነት መመንጫ የመፍትሄ መፈለጊያ የእውነተኛ ዜና መቀያየሪያ መድረክ እንዲያደርገው ማሳሰቢያዬን በኮሚቴው ስም ላቀርብ እወዳለሁ። በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ዙሪያ የተሰበሰቡት ኃይሎችም ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር ጥረቱ በጎ ምላሽ እንዲሰጡ በኮሚቴውና  በራሴ  ስም ጥሪ አቀርባለሁ።

ቸሩ እግዚአብሔር የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር አቅጣጫ ያሳየን።

የስብስቡ ሊቀመንበር

Tuesday, September 14, 2010

ሰላምን መፍጠር እንችላለን

የእግዚብሔር ጸጋና  ቸርነት በሁላችን ላይ ይደር አሜን።

እንዴት ሰነበታችሁ በክርስቶስ ወንድሞችና  እህቶች የሆናችሁ በመላ። ቶሎ እናስነብባችኋለን ብለን ስለዘገየነ ይቅርታ  እንጠይቃለን። እንዴው የሁላችሁንም ጥያቄ  ሊመልስ የሚችል የተቀነባበረ ጽሑፍ ለማውጣት በማሰብ መቆየታችንን ስንናገር ይህ እውነተኛ ምክንያት እንጂ በቂነው ተብሎ አይደለም። ተገናኝተን ለመወያየት ያለውን የጊዜ መጨናነቅ ለመረዳት ደግሞ በፈቃደኝነት የተሳተፉት ሁሉ የሚረዱት ይመስለናል። አሁን ግን ሁኔታው እየተስተካከለ  መጥቶ ከየኮሚቴው የደረሱንን መግለጫዎች ሰሞኑን እንደምናወጣ ቃል እንገባላችሁ ዘንዳ እንወዳለን።  ስለ ትእግስታችሁ ምስጋናችን በድጋሜ ይድረሳችሁ። 

ኮሚቴው

የ E MAIL አድራሻችን

MELEKET4U@GMAIL.COM


Sunday, August 29, 2010

***እንኳን ደህና መጣችሁ!!*** Welcome!!

እንኳን ደህና መጣችሁ!! Welcome!!

ከሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
FROM PUBLIC RELATIONS DEPARTMENT!
ይህንን ድሕረ ገጽ ለማየት እንኳን ደህና መጡ።
የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመፍትሔ ኣፈላላጊ ኮሚቴ፣ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ከሕዝቡ ጋር ለሚያደረገው መገናኛና መወያያ ይሆናል በማለት ይህን ድህረ ገፅ ወይንም ጦማር (BLOG) ከፈተ።  ያልተከለሰና ዘለፋ ያልተቀላቀለበት ቋንቋ ብቻ የምናስተናግድ መሆናችንን እንገልጻለን።
ሰሞኑን በተከታታይ በምናወጣቸው መልእክቶች እንደምትደሰቱ እምነታችን ነው። ይህ ጦማር (blog)እርስ በራሳችን የምንማርበት ዜናዎችንና አስተያየቶችን የምንለጥፍበት፤ የመቀራረቢያ ገጽ ይሆናል ብለን እናምናለን። በትብብራችሁ እናድጋለን፤ በሕብረታችሁ ሰላምን እንፈጥራለን። ፍቅርን ለመፍጠር ለሚደረግ ትግል ሁላችሁም ተባበሩ።

ኮሚቴው