Saturday, September 25, 2010

ሳምንቱን ካጋጠመን

የተከበራችሁ፡ ውድ፡ ምዕመናን፡

     እንደሚታወቀው፡ የቅዱስ፡ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን፡ ችግር፡ መፍትሄ፡ ለማፈላልግ፡ እንድንጥር፡ ከመረጣችሁን፡ ጊዜ፡ አንስቶ፡ የጣላችሁብንን፡ አደራ፡ ለመወጣት በጥንቃቄ፣ በቆራጥነትና፣ በቅንነት፡እየሰራን፡ እንደሆነ፡ ልናረጋግጥላችሁ፡  እንወዳለን።  ችግሩን፡ ለአንዴም፡ ለሁሌም ለመፍታት፡ የምንችለውን፡ ሁሉ፡ በሁሉም፡ አቅጣጫ፡  እየጣርን ነው፡፡ ታዲያ፡ ሰሞኑንም፡ ከቤተክርሰቲያናችን፡ አባላት፡ መካከል፡ የተወሰኑ፡ግለሰቦች፡ ሰላም፡ መስፈን፡ ይኖርበታል፡ ከሚል፡  መርህ፡ በመነሳት፡ አዛውንቶችን፡ አነጋግረው፡ እንደነበረና፡ ሽማግሌዎቹም እንዚህን ቡድኖች ባነጋገሩ ማግስት የኛን ኮሚቴ ለማነጋገር ወስነው መበተናቸውን ለማወቅ ችለን ነበር። ግለሰቦቹን ያነጋገረው፡የሽማግሌዎቹ፡ ኮሚቴ አባላት፡ መካከልም፡ ከፊሎቹ፡ ለቤተክርስቲአናችን፡ ብዙ፡ ግልጋሎት፡ ያበረከቱ፡ በመስራችነታቸው፡ የሚታወቁ ባካባቢያችን፡ የቆዩ፡ የችግሩንም፡ አነሳስ፡ በሚገባ፡ ሲጀመር፡ ጀምሮ፡ የተመለከቱ፡ አንዳሉበትም፡ ለመረዳት ችለናል። ሽማግሌዎቹ፡ እነዚህን ሰላም እንፈልጋለን የሚሉትን ቡድኖች ባነጋገሩ ማግስት፡ሁለት፡ ቀን፡ባልበለጠ፡ ጊዜ፡ውስጥ፡ ተሰብሰበን፡ ከነርሱ፡ ጋር፡ መወያየት፡ እንድንችል፡ በሊቀመ ንበርችን፡ በኩል፡ ጥያቄ፡  አቀረቡ፡፡ አኛም፡ ጊዜ፡ ሳናባክን፡ ተሰብስበን፡ ከሁለት፡ ሰዓት፡ በላይ፡ ጉዳዩን፡ ከሁሉም፡ አቅጣጫ፡ መርምረን፡ ከጉዳቱ፡ ይልቅ፡ ጥቅሙ፡ እንደሚያመዝን፡ በመገንዘብ፡ በአንድ፡ ድምጽ፤ ተቀብለን፡ ሽማግሌዎቹን፡ ሐሙስ፡ በ6፡00PM (9/23/10) ለማነጋገር ተስማምተን በተባለው ሰዓትና ወቅት ሽማግሌዎቹን አነጋግረናል።

 ውይይቱ፡ በአካል፡ በቅዱስ፡ ሚካኤል፡ የስብሰባ፡ አዳራሽ፡ ውስጥ፡የተካያደ ሲሆን መልካም፡ ጅማሮ፡ የታየበት፡ የሁለት፡ ሰዓት ስብሰባ ነበር። ቀጣዩም፡ ስብሰባ፡ የመልክተኞቹ፡ ኮሚቴ፡ ከቤተክርስትያኑ፡ የቦርድ፡ አባላት፡ የይሁንታ፡ ደበዳቤ፡ ከዚያም፡ ለመላው፡ የቅዱስ፡ ሚካኤል፡ ምአመናን፡ በይፋ፡ ከተነገረ፡ በኋላ፡ እንደሚሆን አስታውቀናቸው፡ በቅን፡ መንፍስ፡ ተደምድሟል።

ድ፡ ምአመናን፡ ሆይ!

የቅዱስ፡ ሚካአኤል፤ ችግር፤ የመፍትሄ፤ አፈላላጊ፤ ኮሚቴ፤  የምናደርገውን፤ ጉዞ፤ ሁሉ፤ አንድ፤ በአንድ፤ በጥንቃቄ፤ አንደምናሳውቃችሁ ቃል በገባንው መሰረት ይህንንም ከሌሎች ከመስማታችሁ በፊት ከኮሚቴው እንድትሰሙት በማለት አውጥተነዋል። ወደፊትም አቅማችን፡ በፈቀደው፤ ፍጥነት፤ ሁሉንም ሂደት እንድታውቁት፡ እንደምናደርግ ቃል እንገባላችኋለን።

የሕዝብ፡ ግንኙነት፡ ኮሚቴ፡

የልኡል፡ አግዚአብሔር፡ እረድኤት፡  ይታከልበት!!

Saturday, September 18, 2010

የሰላም ጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

ከስብስቡ ሊቀመንበር የተላከ  መልእክት

የሰላም፤ የአንድነት፣ የፍቅር  ጥረቱ አሁንም እንደቀጠለ  ነው። የምንመኘውን የምንፈልገውን ዘላቂውን ሰላም፤ አንድነት፣ ፍቅር በቤተክርስቲያናችን  ብሎም በሕብረተሰባችን ልናመጣ የምንችለው የተለየዩ  የመፍትሄ  ሃሳቦችን የያዙትን፡ በዳይ ነው የተባለውንም ሆነ ተበድሏል የተባለውን አቀራርበን ውይይት ማድረግ ሲቻልና ብዙሃኑ የተቀበለውን ማስፈጸም ስንችል ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር ለችግራችን ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት ሁላችንም የሚያስማማንን መንገድ የመፈለግ ግዴታ አለብን። ይህ ደግሞ ብስለትን፤ ቅንነትን፤ ሐቀኝነትን፣ መተማመንን ይጠይቃል። ፈረንጆቹ እንደሚሉት(MY WAY OR  THE HIGH WAY ) ወይም እኔ  ያልኩት ካልሆነ እሞታለሁ የሚል አመለካከት ካለ ግን የተነሳንበትን የመወያየቱን መርህ ይገድለዋል።

ይህንን ካልን ዘንዳ!!በዚህም በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተነሳው አለመግባባት ደረጃው ይለይ እንጂ ከቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ዙሪያ "በደል ደረሰብን፣ መብታችን ተነካ፣ መተዳደሪያ ደንቡ ተሸረሸረ፣ የብዙሃን ድምፅ ታፈነ፣ ሃሳባችን አልተስተናገደም ወዘት በማለት የሚያስቡ ግለሰቦች ለችግራቸው መፍትሄ ነው ያሉትን አቅርበው መወያየት ችለዋል። በውይይቱም ተማምነው የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም በቅተለዋል። አስተማማኝ ሁኔታም እስኪፈጸም  ድረስ  የተነሱበትን ዓላም እንደማይስቱ አሁንም ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር እንደሚታገሉ፣ ሁላችንም ይህንን መርህ ከተከተልን ደግሞ ወደ  ነበርንበት መመለሱ ሕልም እንደማይሆን ያምናሉ።  

የአንድ አካባቢ ስብስብ ወይንም በብዙሃን ድምፅ የሚተዳደር አካል ለተለያዩ ሃሳቦች መፍትሄ የሚያገኘው ብዙሃኑ ተስማምቶ በተቀበለው ሃሳብ ሲመራ መሆኑን አንጠራጠርም። ይህንን አማራጭ የሌለውን አካሄድ መከተል ደግሞ ግዴታ ነው እንላለን።  እስከዛሬ በግልም ሆነ በቡድን በጽሑፍም ሆነ በቃል የተነገሩ ሃሳቦች ሁሉ  በእንዲህ ያለ አጠቃላይ ሁሉን አቀፍ ተደጋጋሚ ስብሰባ መቋጨት አለባቸው ብለን እናምናለን።  

የዚህ ጦማር  አጀማመር ደግሞ ያለምንም መደባበቅ በእውነት ላይ ያተኮረ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ሌሎች እንዲረዱት ሃሳቦችን ማንሸራሸር እንዲቻል ከሚያገኘው ጭብጥ በመነሳት አንባቢው ፍርድ መስጠት እንዲችል ለመርዳት ጭምር ነው።

የጦማሩ ባለቤቶች በ 200አባላት የተመረጠው የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴ ሲሆን፣ ኮሚቴው እስካሁን ያከናወነውን እያደነቅሁ በዚህም መስክ ጥሩ ተግባር እንደሚያሳይ ጥርጥር የለኝም። አባላቱም የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ጦማሩ የእውነት መመንጫ የመፍትሄ መፈለጊያ የእውነተኛ ዜና መቀያየሪያ መድረክ እንዲያደርገው ማሳሰቢያዬን በኮሚቴው ስም ላቀርብ እወዳለሁ። በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ዙሪያ የተሰበሰቡት ኃይሎችም ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር ጥረቱ በጎ ምላሽ እንዲሰጡ በኮሚቴውና  በራሴ  ስም ጥሪ አቀርባለሁ።

ቸሩ እግዚአብሔር የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር አቅጣጫ ያሳየን።

የስብስቡ ሊቀመንበር

Tuesday, September 14, 2010

ሰላምን መፍጠር እንችላለን

የእግዚብሔር ጸጋና  ቸርነት በሁላችን ላይ ይደር አሜን።

እንዴት ሰነበታችሁ በክርስቶስ ወንድሞችና  እህቶች የሆናችሁ በመላ። ቶሎ እናስነብባችኋለን ብለን ስለዘገየነ ይቅርታ  እንጠይቃለን። እንዴው የሁላችሁንም ጥያቄ  ሊመልስ የሚችል የተቀነባበረ ጽሑፍ ለማውጣት በማሰብ መቆየታችንን ስንናገር ይህ እውነተኛ ምክንያት እንጂ በቂነው ተብሎ አይደለም። ተገናኝተን ለመወያየት ያለውን የጊዜ መጨናነቅ ለመረዳት ደግሞ በፈቃደኝነት የተሳተፉት ሁሉ የሚረዱት ይመስለናል። አሁን ግን ሁኔታው እየተስተካከለ  መጥቶ ከየኮሚቴው የደረሱንን መግለጫዎች ሰሞኑን እንደምናወጣ ቃል እንገባላችሁ ዘንዳ እንወዳለን።  ስለ ትእግስታችሁ ምስጋናችን በድጋሜ ይድረሳችሁ። 

ኮሚቴው

የ E MAIL አድራሻችን

MELEKET4U@GMAIL.COM