የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰላም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ UNITED ST. MICHAEL CHURCH PEACE RESOLUTION SEEKERS COMMITTEE
1-23-2011
ጠቅላላ የምዕመናን ስብሰባ
ከተሰጡትም ገንቢ አስተያየቶችና መልዕክቶች መካከል፤
ሀ. የኮሚቴው ዋና ሥራ የሆነው የሕግ አገልግሎት ጉዳይን በተመለከት መሰረታዊ ጥያቄዎችና ዓላማዎች ግልፅና አጭር በሆነ መልክ ለምዕመናን መግለጫ እንዲሰጥ።
ለ. የመልአከ ሣህልን በሥራ ጉዳይ ምክንያት ወደ ሌላ ግዛት መሄዳቸውን አስመልክቶ በ 1-28-2011 በሚደረገው የሽኝት ዝግጅት ላይ ከዓርብ ጉባኤ ጋር በመቀናጀት አሰኛኘት እንዲደረግላቸው።
ሐ. በቅርቡ በሚካሄዱት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች 2-7-2011፣ በ3 ፒ ኤም እና 2-10-2011፣ በ9 ኤ ኤም ላይ መገኘት የሚችሉ ምዕመናን አንዲገኙ።
መ. “ቤተክርስቲያን ተከሷል” የሚባለው የተዛባ ውዥንብር የሚወገድበት ትክክለኛው የፍትሕ ጥረት ለምዕመናኑ በመግለፅ የሚረዱበት መንገድ እንዲፈጠር።
ሠ. በዓርብ ጉባኤ እየተዘጋጀ ባለው ሦስተኛ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ኮሚቴው ትብብሩን እንዲያደርግና መድረኩንም በመጠቀም ለሕዝቡ መልእክት እንዲያዘጋጅ።
ረ. የሕግ ጉዳዩን በተመለከተ ለሚያስፈልጉት የኃሳብና የገንዘብ ዕርዳታ ቅንጅትና ትብብር በመላ ምዕመናኑ የሚካሄድበትን።
ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
No comments:
Post a Comment