ውድ ምዕመናን! የእግዚአብሔር ሰላምታችንን እናቀርባለን።
ምንም ጊዜው ቢራዘም፣ የሰላም ኮሚቴ ሥራውን እየሠራ ነው። የሕዝብንም አደራ እንደጠበቀ ነው። ይህ በግንቦት 2010፣ ከ200 ያላነሱ ምዕመናን የመረጠው 9 የሰላም ኮሚቴዎች ሥራችን ወደ ማገባደድ ላይ ናቸው። ሥራቸው ተፈፀመ የሚያሰኘው ሪፖርታቸውን ለታዘዙት አደራ ከፈፀሙ በኋላ እስከሚያቀርቡና ምዕመናኑ እስከሚያሰናብታቸው ድረስ ነው። ይኸንንም ለመፈፀም የሚያስፈልገው፣ ከአንድና ከሁለት ጊዜ በማይበልጥ፣ ከኮሚቴና ከንዑስ ኮሜቴዎች ጋር ስብሰባ ካደረገ በኋላ ታላቅ የሕዝብ ጥሪ እንደሚያደርግ ለምዕመናን ለማሳሰብ እንወዳለን። ትዕግሥት እንደማር ወለላ ትጣፍጣለች።
የሰላም ኮሚቴ
የሕዝብ ግኑኝነት ክፍል።
No comments:
Post a Comment